=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ንባብ በህይወታችን ልናዳብረው እና ልናሳድገው የሚገባ እጅግ ጠቃሚ ክህሎት ሲሆን ጠቀሜታውም በትምህርታችን ወይም በተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ኑሯችን ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ክህሎት ነው።
የሚከተሉት ጠቇሚ ነጥቦች የንባብ ጊዜያችነን እና የንባብ ክህሎታችነን ለማሳደግ የሚረዱን ናቸው።
ΩΞ ማንበብ የሚያስደስተንን ነገር እና ሊጠቅመን የሚችል ነገር ለይተን እንወቅ
ΩΞ ቇሚ የንባብ ወይም የጥናት ጊዜ ይኑረን
ΩΞ አዘውትረን ወደ ላይብረሪዎች ጐራ እንበል
ΩΞ የኔ የምንላቸው መጽሐፎች ይኑሩን
ΩΞ አዲስ የሆነን ነገር ለማወቅ ጉጉት ይኑረን
ΩΞ የአንድ ፅሁፍ ሃሳብ ሊገባን ወይም ትርጉም ሊሰጠን ካልቻለ እውቀት ያለው ሰው እንዲገልፅልንና እንዲያብራራልን እንጠይቅ
ΩΞ ሃሳቡን ከተረዱት ሰዎች ከአስተማሪዎቻችን ጋርም ሆነ ከጏደኞቻችን ጋር እንወያይበት
ΩΞ ቁልፍ የሆኑ ሃሳቦችን በማስታወሻ እንያዝ
ΩΞ ጥያቄ እጥር ምጥን ባለመልኩ የመጠየቅ ልምድ ይኑረን
ΩΞ በማስታወሻ የያዝናቸውን ነጥቦች ከልሰን በማየት ያልገባንን ነገር በጥያቄ መልክ በማቅረብ ለበለጠ ንባብ እራሳችነን እናዘጋጅ
ΩΞ የምናነበውን ነገር መፃፋችን እንድናስታውሰው ይረዳናነልና እየያነበብን እንፃፍ
ΩΞ ያነበብነውን ነገር ምን ያህል እንደተረዳ ነው ለማወቅ እራሳችነን የተወሰኑ ጥያቄዎችን እንጠይቅ
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|